Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አልፈዋል። እየተካሄደ በሚገኘው የቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020 የ3000 የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል። መቅደስ አበበ በ9፡23.95 3ኛ ወጥታ ስታልፍ፥ ዘርፌ ወንድማገኝ በ9:20.01 4ኛ ወጥታ ያለፈች ሲሆን፥ ሎሚ ሙለታ በ9:45.81 10ኛ ወጥታ ማጣሪያውን አላለፈችም። ማጣሪያውን…
Read More...

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለ10 ሺህ ሜትር የወንዶች አሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ፡፡ በዚህ መሰረትም ርቀቱን በ27 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ ያጠናቀቀው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ተረክቧል፡፡ የኡጋንዳ አትሌቶች ጆሽዋ ቺፕቴጌ እና…

ታንዛኒያ የሴካፋ ከ23 አመት በታች ዋንጫ አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ሲካሄድ የቆየው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ23 አመት በታች እግር ኳስ ውድድር በታንዛኒያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ዛሬ በፍጻሜ ጨዋታ ከብሩንዲ ጋር የተጫወተችው ታንዛኒያ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አሸናፊ ሆናለች፡፡ መደበኛው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ያለምንም ጎል አቻ…

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል፡፡ ዑጋንዳውያኑ ጆሹዋ ቺፕቴጌና ጃኮፕ ኪፕሊሞ አትሌት ሰለሞን ባረጋን ተከትለው በመግባት የብር…

በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ የ5000 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል። በመጀመሪያው ምድብ ሰንበሬ ተፈሪ 3ኛ፣ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ 4ኛ ሆነው አጠናቀዋል። ከሁለተኛው ምድብ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ ማጣሪያውን አልፋለች። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 8:00 ሰዓት የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ ቀን 8:00 ሰዓት ጀምሮ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ እና በርሁ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ለማስመዝገብ ውድድራቸውን ያካሂዳሉ፡፡ በተመሳሳይ በሴቶች 5 ሺህ ማጣሪያ እጅጋየሁ ታዬና ሰንበሬ ተፈሪ በምድብ 1…

ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸውን አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ላይ በተካሄደው የቶኪዮ 2020 አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ እንዲሁም የ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፈዋል፡፡ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ለሜቻ ግርማ በ8 ደቂቃ 9 ሰከንድ ከ83 ማይክሮ ሰከንድ ሰዓት 1ኛ እንዲሁም ጌትነት ዋለ በ8…