Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኘች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኘች፡፡ በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሃሰን ለኔዘርላንድስ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ ኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ለሀሃገሯ አስገኝታለች፡፡ በውድድሩ የተሳተፈችው  አትሌት እጅጋየሁ ታዬ አምስተኛ በመሆን ውድድሩን ስታጠናቅቅ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ  ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን ጨርሳለች፡፡…
Read More...

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 9፡15 በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡ በዚህም ለሜቻ ግርማ  ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ  ሲያስገኝ  ጌትነት ዋለ ውድድሩን በአራተኝት አጠናቋል፡፡ ሞሮኳዊው አትሌት ሶፊያን ኤል ባካሊ ውድድሩን ሲያሸንፍ ኬንያዊው…

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ የሚጠበቁ የፍፃሜ ውድድሮች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ ከሰዓት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ፡፡ በዚህም ከቀኑ 9:15 ሰዓት ላይ 3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ ይሮጣሉ፡፡ በተመሳሳይ 9፡40 ሰዓት በሴቶች 5000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና እጅጋየሁ ታዬ ለኢትዮጵያ ወርቅ ለማምጣት እንደሚወዳደሩ ከኢትዮጵያ…

አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ1500 ሜትር ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ1500 ሜትር ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል። በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ በሶስት የተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ሲያልፉ ድርቤ ወልተጂ ማጣሪያውን ማለፍ…

መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አልፈዋል። እየተካሄደ በሚገኘው የቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020 የ3000 የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል። መቅደስ አበበ…

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለ10 ሺህ ሜትር የወንዶች አሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ፡፡ በዚህ መሰረትም ርቀቱን በ27 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ ያጠናቀቀው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ተረክቧል፡፡ የኡጋንዳ አትሌቶች ጆሽዋ ቺፕቴጌ እና…

ታንዛኒያ የሴካፋ ከ23 አመት በታች ዋንጫ አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ሲካሄድ የቆየው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ23 አመት በታች እግር ኳስ ውድድር በታንዛኒያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ዛሬ በፍጻሜ ጨዋታ ከብሩንዲ ጋር የተጫወተችው ታንዛኒያ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አሸናፊ ሆናለች፡፡ መደበኛው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ያለምንም ጎል አቻ…