Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያይቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ዛሬ ተከናውኗል። በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ወልቂጤ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሰበታ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ከ14 ጨዋታዎች 15 ነጥብ ብቻ በመያዝ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ27 ነጥቦች ሲመራ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ26…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት በክልል ከተማዎች በዛሬው ዕለት 5 ጨዋታዎች ተካሂደዋል። በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭ አንድ ነጥብ በማግኘት በ27 ነጥብ የአንደኝነት ደረጃውን ሲያስጠብቅ በተመሳሳይ ፋሲል…

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በይፋ ተለኮሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በአዲስ አበባ  በይፋ ተለኮሰ። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም የኦሎምፒክ ቡድኑ የቶክዮ 2020 የመጀመሪያውን ችቦ በይፋ ለኩሰዋል። በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ ኢትዮጵያውያን በተባባረ አንድነትና ህብረት ወደ ላቀ ብልፅግና እንደርሳለን፤ ኢትዮጵያ ብዙ…

በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። ሀዋሳ ከተማን በትግራይ ስታዲየም ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ 5 ለ1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል። የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ኦኪኪ አፎላቢ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ አስቆጥረዋል። የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ…

ማንቼስተር ሲቲ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለሁለት አመት ታገደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ሲቲ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እንዳይሳተፍ ታገደ። ክለቡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን የገንዘብ አስተዳደር (የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይን) አላከበረም በሚል ነው እገዳው የተጣለበት። እገዳውን ተከትሎም ክለቡ በቀጣዮቹ ሁለት አመታት በትልቁ የክለቦች ውድድር…

ውጤት ላስመዘገቡ አትሌት እና አሰልጣኞች ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 ኤፍ.ቢ.ሲ) በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች እና ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው። የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማቱ በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች፣ በ6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሻምፒዮን፣ በ1ኛው የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው አትሌቲክስ…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ አቻ ተለያዩ  

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ ፍቅረየሱስ ተክለብርሀን በ29ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። የወልቂጤ ከተማን ግብ…