Fana: At a Speed of Life!

በፕራግ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የፕራግ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ።

በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2፡08፡45 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሄርጳሳ ነጋሳ እና አባይነህ ደጉ አምስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት በዳቱ ሂርጳ 2:23:41 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች።

አትሌት በዳቱን በመከተል ኬንያዊቷ ዶርካስ ጄፕቺርቺር ሁለተኛ ስትሆን ከሶስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ ባለው ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት በውድድሩ የነበራቸውን የበላይነት አሳይተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.