Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት አባዲ ሃዲስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው የ22 ዓመቱ ወጣት አትሌት አባዲ ሀዲስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አትሌት አባዲ በኦሎምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በመከወል በተለያዩ ውድድሮች ተሳትፏል። አባዲ ሀዲስ በመቐለ ሃይደር ሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት ቆይቶ ጥር 26 ቀን…

ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኙን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሪሚየር ሊጉ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ስምዖን አባይን አሰናበተ። ድሬዳዋ ከተማ ከባለፉት 12 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማግኘት ካለበት 36 ነጥብ ውስጥ 13 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚጫወቱ 16 ክለቦች 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በቡድኑ ውጤት…

የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ። በመድረኩ ላይ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ፣ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ስለ ስፖርት ህክምና እና የፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥርና ክትትል ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማና ሰበታ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል። ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማን ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎል የፕሪሚየር ሊጉን ኮኮብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ሙጅብ ቃሲም በ24ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።…

የፊፋው ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ዋንጫ በ4 ዓመት አንድ ጊዜ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የመርሃ ግብር ማስተካከያ እንዲደረግ እንደሚፈልጉ ገለፁ። ፕሬዚዳንቱ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ በ4 ዓመት አንድ ጊዜ እንዲካሄድ ፍላጎት አላቸው። ኢንፋንቲኖ በሞሮኮ ራባት በእግር ኳስ…

ጃፓን የኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን የኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር የተቻላትን ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሺንዞ አቤ ለዚህም ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒስትሩ ሰኢኮ ሃሺሞቶ…