Fana: At a Speed of Life!

በመጋቢት ወር ከ27 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጋቢት ወር ብቻ ከ27 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በወሩ 27 ቢሊየን 219 ሚሊየን 961 ሺህ 375 ነጥብ 3 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ መስራቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በዚህም 27 ቢሊየን 130 ሚሊየን 353 ሺህ 57 ነጥብ 33 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል፡፡
ይህም የዕቅዱን 99 ነጥብ 67 በመቶ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6 ቢሊየን 117 ሚሊየን 683 ሺህ 46 ነጥብ 56 ብር ብልጫ ወይም 29 ነጥብ 11 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ነው የተባለው።

ገቢው ከሀገር ውስጥ ታክስ 14 ቢሊየን 147 ሚሊየን 24 ሺህ 628 ነጥብ 95 ብር እንዲሁም ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 12 ቢሊየን 983 ሚሊየን 328 ሺህ 428 ነጥብ 38 ብር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.