Fana: At a Speed of Life!

በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ስራ እየሰራን ነው – ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ከዚህ በፊት የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል።
የግብርና ልማታችን የእድገታችን መሰረት ስለሆነ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ጠቁመው÷ በግብዓትና በገበያ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በአርሲ ዞን በሎዴ ሄጦሳ ሁሩታ ቀበሌ በመገኘት የሽንኩርት ማሳቸው ላይ ያገኟቸውን አርሶ አደሮች አበረታትተዋል።
በተጨማሪም÷ በአርሲ ዞን ሎዴ ሄጦሳ ወረዳ መልካ ጀቢ ቀበሌ በኩታ ገጠም የተዘራ የስንዴ ሰብል የጎበኙ ሲሆን÷ የጋቢ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ ዘንድሮ በክልሉ ከሚመረተው የስንዴ ምርት ውስጥ 74 በመቶ በኩታ ገጠም የሚመረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.