Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ተሰራጭቷል

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2012 የበጀት አመት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መሰራጨቱን የክልሉ ኀብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በበጀት ዓመቱ 6 ሚሊየን 111 ሺህ 561 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት ታቅዶ የነበረ ሲሆን እስካሁን ወደ መጋዘን የገባው 5 ሚሊየን 282 ሺህ 774 ኩንታል ወይም ከእቅዱ 86 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑን ኢጀንሲው አስታውቋል፡፡

ከዩኒየኖች እና መሠረታዊ ኀብረት ሥራ ማኀበራት መጋዘን የከረመውን በመጨመር 5 ሚሊየን 950 ሺህ 312 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በ145 ወረዳዎች ለሚገኙ 1 ሺህ 388 ሁለገብ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት በዩኒየኑ በኩል የማጓጓዝ ሥራ ተከናውኗል ተብሏል፡፡

ለአርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ እጅ በእጅ እና በብድር የተሰራጨ እና አሁንም በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝም ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.