Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበበ በአንድ ጀንበር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ ተተከለ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)  በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀንበር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ1 ሚሊየን በላይ የከተማ ነዋሪዎች መሣተፋቸውን ምክትል ከንቲባው በሰጡት መግለጫ ላይ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀንበር 2 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ነው ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኝ የተተከለው።

በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስሩ በአንድ ጀምበር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ላይ ለተሳተፉ  ዜጎች ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የችግኝ መትከያ ወቅት አጋማሽ ላይ በምንገኝበት በዚህ ጊዜ፣ የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ የሚጠብቀውን ለማሳካት ስለ ተጋችሁ አመሰግናችኋለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን በሙሉ  ከታሰበው ዓመታዊ ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ምላሽ  እንዲሰጡ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም በአብሮነት እናሳካዋለን ነው ያሉት።

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀንበር 2 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች ተካሂደዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቦች እና  የከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.