Fana: At a Speed of Life!

በአዋሽ ቢሾላ ማሰልጠኛ ማእከል ለ2ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣መስከረም፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዋሽ ቢሾላ ማሰልጠኛ ማእከል በሁለተኛ ዙር ለከተቱት ምልምል ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ መረሐ ግብር ተከናወነ።
በመርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት የስራ መመሪያ የሰጡት፥ የዋሽ ቢሾላ እና የቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች የበላይ አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ዲሪባ መኮንን ናቸው።
ጀነራል መኮንኑ በሰጡት የስራ መመሪያ ፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በስልጣን በቆየባቸው ጊዜያት በህዝቦች ላይ ግፍና በደል እየፈጸመ ቆይቷል።
አሁንም የህዝብና የመንግስት ንብረትን ከመዝረፍና ህጻናትን ከመድፈር አልፎ በእንስሳት ላይም ሳይቀር ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በመፈጸም ላይ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት የዚህን አሸባሪ ቡድን እኩይ ተግባር ለማክሸፍና ህግን ለማስከበር እየወሰደ ላለው ዘመቻ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር በመቀላቀል የሚጠበቅባችሁን ለማበርከት ስለመጣችሁ ልባዊ አክብሮቴን አቀርብላችዋለሁ ብለዋል።
የአዋሽ ቢሾላ ማሰልጠኛ ማእከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል ተረፈ ጩሪሶ በበኩላቸው ፥ በማሰልጠኛ ት/ቤቱ ቆይታችሁ የሚሰጣችሁን ወታደራዊ ስልጠና በእልህና ሞራል በመሰልጠን አገር የማዳን አላማ ከግብ ማድረስ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።
በመክፈቻ መርሀ-ግብሩ ላይ በስራ አፈጻጻመቸው ውጤት ላስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊቱ አባላት በሌተናል ጀነራል ድሪባ መኮንን ማዕረግ የማልበስ ስነ-ስርአት መፈጸሙን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
322
Engagements
Boost Post
298
9 Comments
15 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.