Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በጎርፍ የተከበቡ 25 ሰዎችን መታደግ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፍየል ቤት አካባቢ በተሽከርካሪ ውስጥ እንዳሉ በጎርፍ ተከብበው የነበሩ 25 ወገኖችን ጉዳት ሳይደርስባቸው መታደግ ተቻለ፡፡
በሌላ በኩል ከቀኑ 7 ሠዓት ተኩል ላይ በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 መሳለሚያ የካቲት 23 ትምሕርት ቤት አካባቢ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የነበረ ዕድሜው 35 የሚገመት ግለሰብን በሕይወት ማትረፍ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.