አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የትንሳኤ በዓል የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የትንሳኤ በዓል ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሰላም፣ የደስታና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገለጹ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በነገው ዕለት የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም በዓሉ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን የሰላም፣ የደስታና የመተሳሰብ እንዲሆን መመኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡