Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በበጎ ፈቃድ ተግባራት 7 ቢሊየን ብር የልማት ስራ መከናወኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛው የዓለም የበጎ ፈቃደኝነት ሪፖርት በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ “እኩል እና ሁሉን አቀፍ ማህበራትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ የየሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በበጎ ፈቃደኝነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሸናፊነቱን ለማስቀጠልና ለበጎ ፈቃደኞች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው።

በዚህም በኢትዮጵያ 21 ሚሊየን በላይ ዜጎች ባከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ ተግባራት 7 ቢሊየን ብር የሚገመት የልማት ስራ መከናወኑን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት።

በኢትዮጵያ በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራትም 7 ቢሊየን ብር የሚገመት የልማት ስራ መከናወን መቻሉን ዶክተር ኤርጎጌ ጠቁመዋል፡፡

በመክፈቻ መርሐ ግብሩ በዘንድሮ የዓለም የበጎ ፈቃደኝነት ሪፖርት ግኝቶች ላይ ቀጣይነት ያለው ቀጠናዊ ውይይት ለመጀመርና ተነሳሽነት ለመፍጠር በሪፖርቱ ላይ የተካሄደውን ዓለም አቀፍ ውይይቶች እና በአፍሪካ ውስጥ ባሉ ባለድርሻ አካላት ፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ተቋማት መካከል ግንዛቤን ለማሳደግ ወስዷል።

በመርሐ ግብሩ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የተመድ የስራ ኃላፊዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እንዲሁም ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃ ፡-ኢዜአ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.