Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች በክልሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች በጥናትና ምርምር የተደገፈ እገዛ እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ጥምረት ዓመታዊ ጉባኤ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡
የጥምረቱ ሠብሳቢና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ እንደተናገሩት፥ ጥምረቱ ከተቋቋመት በ2007 ዓ.ም ጀምሮ ለሃገር ልማት አጋዥ የሆኑ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በተለይም በአሁኑ ወቅት በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ፣ በቦረና በድርቅ ለተጐዱ እና በመተሀራ በጐርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በኦሮሚያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በጋራና በተናጠል የተለያየ ሰብኣዊ ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል የሱፍ በበኩላቸው፥ የጥምረቱ አባላት በጋራና በተናጠል ሀገሪቱ የተጋረጠባትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመታደግ ስናበረክት የቆየነውን የገንዘብ፣ የቁሳቁስ፣ የሞራልና የደም ልገሣ አስተዋፅዖ በተጨማሪ በሃገር ግንባታ ላይ ምሁራዊና ሞያዊ አስተዋፅዖ ማበርከታችንን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።
በ2007 ዓ.ም የተቋቋመው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ጥምረት በአሁኑ ወቅት 14 ዩኒቨርሲቲዎችና 16 ኮሌጆችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በተሾመ ኃይሉ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.