Fana: At a Speed of Life!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና መሰጠቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

 

ስልጠናው በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሚኒስቴሩ፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነው እየሰጠ የሚገኘው።
 
በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንደገና ለማስጀመር የፖሊስ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
 
ወይዘሮ ፍሬአለም ቫይረሱ እየተስፋፋ ከመሆኑ አኳያ ጥንቃቄ ማድረግ እና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የሰራዊት አባላት ጠንክረው በመስራት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
 
የፖሊስ አባላት ጸጥታ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የሚፈጠሩ ስህተቶችን ወደ ትምህርት በመቀየር መካሪም አስተማሪም መሆን አለባቸውም ነው ያሉት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.