Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የከተራና ጥምቀት በዓል ያለ የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የከተራና ጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ እንደገለጹት በክልሉ በዓሉ በሠላም እንዳይከበር የሚፈልጉ ኃይሎች ችግር እንዳይፈጥሩ በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

ህዝቡ በተለይም ወጣቱ የፀጥታው ባለቤት ሆኖ እንዲሰራም ቀደም ብሎ በተዘጋጀው የበዓል ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይልም አስፈላጊው ስምሪት ተሰጥቶት በመቀናጀት የአካባቢውን ፀጥታ እያስከበረ የሚገኝ ሲሆን፤ በየአካባቢው የሚገኙ ወጣቶችም በራሳቸው ተነሳሽነት ዝግጅት አድርገው ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን የአካባቢያቸውን ፀጥታ እየጠበቁ እንደሚገኙም አስረድተዋል።

በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ህብረተሰቡ ሠላሙን በመጠባበቅ በሠላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የነቃ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለፀጥታው መጠበቅ አጋዥ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ህዝቡ በዓሉን ሲያከብር አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.