Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ግንባር የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ የቋመጠው ትህነግ በወሎ ግምባር አልተሳካለትም

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡድኑ በደቡብ ጎንደር ግንባር የዋናውን ግንባር ሃይል ለማሳሳት ወደ ምስራቅ እያሰፋ ሰርጎ ለመግባትና የደሴና ሀይቅ ከተሞችን ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት እንደከሸፈ የወሎ ግምባር ኮማንድ ፓስት አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም ተናግረዋል።
ሌተናል ጀኔራል ሀሰን በግንባሩ ለሚገኙት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን እንደገለጹት÷አሸባሪው ህወሓት በሰው ሃይል ብልጫ ወስዶ ጥሶ ለማለፍ እና ለመቆጣጠር ቢፍጨረጨርም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው የመከላከል እርምጃ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።
በዚህ ሰአት ቡድኑ ወደ ኃላ ለመሸሽ እንደተገደደ ያነሱት ሌተናል ጄኔራል ሀሰን÷ የገባባቸውን አካባቢዎችም ጥሎ ፈርጥጧል ነው ያሉት።
የደቡብ ወሎ አርሶ አደር መከላከያ ቦታዎቹን እስኪቆጣጠር ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓልም ብለዋል።
በዚሁ ግምባር የሽብር ቡድኑ የሞት ሽረት ትግሉን አድርጓል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ሀሰን÷ አሁን ላይም ሃይሉ ተበታትኖ ዳግም ወደ ጥቃት የማይንደረደርበት ሁኔታ ላይ እንዳለ አረጋግጠናል ነው ያሉት።
በኤፍ ቢ ሲ ጋዜጠኞች ቡድን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.