Fana: At a Speed of Life!

በETRSS 1 ሳተላይት ማምጠቅ ስራ ላይ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በETRSS 1 ሳተላይት ማምጠቅ ስራ ላይ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ሰጠ።

ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሳተላይት ታህሳስ 10 ወደ ህዋ ማምጠቋ የሚታወስ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማምጠቅ ስራ ላይ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ሰጥቷል።

በእውቅና መስጠት ዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ፥ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት የስፔስ ሳይንስ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፉን ለማሳደግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሚጠበቅበትን ሁሉ ይወጣል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሳተላይት ያመጠቀችበት ቀን የኢትዮጵያ ስፔስ ቀን ሆኖ ይከበራልም ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የቀድሞው የኢኖቬሽንናቴክኖሎጂ ሚኒስትር የአሁኑ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ ስፔስ ሳይንስ ለሁሉም ዘርፎች ወሳኝ በመሆኑ ሌሎች ሳተላይቶችን እና የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ የተጀመረው ስራ ሊጠናከር ይገባማለታቸውን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.