Fana: At a Speed of Life!

ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ድርብ በዓል እያከበረች ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ድርብ በዓል እያከበረች ትገኛለች፡፡

ከተማዋ አንድም አሸባሪው ህወሃት ድል ተደርጎ ከጨለማና ከአፈና ነፃ የወጣችበትን የሰላምና የድል በዓል፥ ሌላም የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ዋዜማ በታላቅ ድምቀትና በሰላም እያከበረች መሆኗን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ ማምሻውን ከስፍራው ዘግቧል፡፡

በዓሉን ለማክበር ከሀገር ውስጥና ከውጭ አገራት ወደ ላሊበላ የተጓዙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ዋዜማውን በድምቀት እያከበሩ ነው፡፡

ነዋሪዎቿም እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ፍቅርና ባህል በደስታ ተቀብለው በማስተናገድ ላይ ሲሆኑ፤ ሃይማኖታዊ ዜማዎችና አስተምህሮት እየተሰጠም ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.