Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቋሚነት ወገኖቻቸዉን እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ከእናት አገራቸዉ ኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ እና በቋሚነት ወገኖቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በስዊድን፣ ፖላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚሸፍናቸው በስዊድን ፣ ፖላንድ ፣ ኖርዌይ ፣ ዴንማርክ እና ፊንላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በ”ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ” ማህበር አስተባባሪነት በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይና የተጎዱ ወገኖችን በቀጣይነት ለመደገፍ የሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ለሀገራዊ ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የውይይት መድረኩን ያስተባበሩትን በማመስገን በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ከእናት አገራቸዉ ኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ እና ቋሚ በሆነ መንገድ ወገኖቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.