Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የሦስት ሚሊየን ብር መጻሕፍት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ሦስት ሚሊየን ብር የሚያወጡ መጻሕፍትን አበረከተ።

መጻሕፍቱን ያስረከቡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ፥ ኢትዮጵያ የመጻሕፍት ሀገር ብትሆንም የቤተ መጻሕፍት ሀገር እንዳልነበረች ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ያመጣነው የሦስት ሚሊየን ብር መጻሕፍትም በኢትዮጵያውያን የተጻፉና በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት የታተሙ የትምህርት መርጃ፣ የልቦለድ፣ የታሪክና የተለያየ ዘውግ ያላቸው መጻሕፍት ናቸው ብለዋል።

በቀጣይም በቋሚነት አዳዲስ መጻሕፍት ሳይዘገዩ የሚገቡበት እንዲሆንም ከአብርሆት ጋር በቅርበት እንሰራለን ነው ያሉት።

መጻሕፍቱን የተረከቡት የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ ጥበባት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው÷ የብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ማበርከቱ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።

በሐይማኖት እያሱ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.