Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው “የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ መከታተያና መቆጣጠሪያ ሲስትም” አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ (ኢመደኤ)“የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከታተያና መቆጣጠሪያ ሲስትም” አዘጋጀ።

አዲስ የተዘጋጀው ሲስተም ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ሥርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጊዜ የማይሰጥ ርብርብ የሚያግዝ መሆኑንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የተዘጋጀው ሲስተም የተለያዩ መረጃዎችን የሚሰጥ መሆኑን  ያስታወቀው ኤጀንሲው፤

ከእነዚህ መካከልም፦

  • ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ወቅታዊ የኮሮናቫይረስ መረጃዎችን ለመከታተል፤
  • ገላጭ በሆኑ የቦታ ማሳያ መረጃዎች ለማየት፤
  • ስለ ኮሮናቫይረስ ምልክቶች፣ ጥንቃቄዎች፣ ህክምናዎች እና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት፤
  • ዜጎች በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ጥርጣሬዎች ሪፖርት ለማድረግ፤
  • የተለያዩ ሙያ እና አቅም ያላቸውን በጎ ፈቃደኞች ለመመዝገብ፤
  • የተለያዩ እርዳታዎችን (በአይነትም ሆነ በገንዘብ) ለመሰብሰብ፤
  • ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ መረጃ ያላቸውን ምንጮችን (ሊንኮችን) ለመጠቆም፤
  • አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ-ልማቶችን (ሆስፒታል፣ ፋርማሲ፣ ፖሊስ ጣቢያ) ለማመላከት፤

እንዲሁም ሌሎችን መረጃዎች ለማሰራጨት የሚያገለግል ሲስተም ነው፡፡

የመከላከያና መቆጣሪያ ሲስተሙ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለውን የከፋ ሁኔታ ከወዲሁ ለመከላከልና ጥንቃቄ ለማድረግ በሚል የተዘጋጀ ሲሆን፥ በነገው ዕለት መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ይሆናል።

በዚሁ አጋጣሚ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሃገራዊ ርብርብ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ (ኢመደኤ) የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.