Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ማለዳ ከአሜሪካና ካናዳ የገቡ ዳያስፖራዎች 17 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አሰባሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና ከካናዳ ቶሮንቶ ለእናት ሀገር ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በርካቶች ማለዳውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ዳያስፖራዎች በጉዟቸው ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ ገንዘብ በማሰባሰብ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ ነው።

ዛሬ ማለዳ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ በገባው በረራ ታዋቂ ግለሰቦችና ተሳፋሪዎች 12 ሺህ የአሜሪካ ዶላር አሰባስበው ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከካናዳ ቶሮንቶ ወደ ሀገር ቤት እየመጡ ያሉ መንገደኞች 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በማሰባሰብ በአይዞን ኢትዮጵያ አካውንት ገቢ አድርገዋል።

ዳያስፖራው በሀገር ቤት ቆይታው በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት ወገኖችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በሚችሉት ሁሉ እንደሚያግዙ ነው የተመላከተው፡፡

ከሀገራቱ የመጡ ዳያስፖራዎች በጉዟቸው ወቅት ያሰባሰቡትን የገንዘብ ድጋፍ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ገቢ እያደረጉ ይገኛል።

በቆንጂት ዘውዴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.