Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶች በሆቴሎች ጥሩ አቀባበልና መስተንግዶ ይጠብቃቸዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶች በሆቴሎች ጥሩ አቀባበልና መስተንግዶ እንደሚደረግላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሆቴል ባለንብረቶች ማሕበር አስታወቀ።
ለኢሬቻ በዓል ከውጭና ከአገር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው ከ400-500 እንግዶች አዲስ አበባ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የማሕበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አመሃ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ሆቴሎች በዓላቱን ለማክበር የሚመጡ የውጭና የአገር ውስጥ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቀዋል፡፡
የአገር ውስጥና የውጭ እንግዶች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር በዓሉን ሲያከብሩ የተሻለ መስተንግዶና ጥሩ አቀባበል ይጠብቃቸዋልም ነው ያሉት፡፡
ሆቴሎች ለሀገር ውስጥ ገበያም ትኩረት በመስጠት የዘርፉን አገልግሎት ለማሳደግ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች ለውጭ እና ለአገር ውስጥ እንግዶች እኩል ትኩረት እንዲሰጡም ጠይቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በዘርፉ የሚፈለገውን እድገት ለማምጣትና የተለያዩ አማራጮችን ለማየት አገልግሎቱን ማስፋት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያዊያን ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው አገራቸውን የሚጎበኙበትና በዓላትን የሚታደሙበት ልምድ እንዲያካብቱ ለማድረግ የሆቴሎች መስተንግዶ ወሳኝ መሆኑንም አቶ አመሃ ገልጸዋል።
የሆቴል ባለንብረቶች ከባህልና ቱሪዝም፣ ከአስጎብኝዎችና ከተሽከርካሪ አከራይ ድርጅቶች ጋር በመሆን እንግዶች በሆቴሎች የሚኖራቸውን የቆይታ ጊዜ ምቹ ለማድረግ በቅንጅት እየሰሩ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.