Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የብሉ ናይል ግዛት የጋራ የድንበር ልማት ትብብር ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን የብሉ ናይል ግዛት የጋራ የድንበር ልማት ትብብር ውይይት በአሶሳ ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡
 
በሱዳን የብሉ ናይል ግዛት ፕሬዚዳንት ጄኔራል አህመድ አልዑምዳ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ለውይይቱ ትናንት ማምሻውን ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ መግባቱ ይታወሳል፡፡
 
ልዑካኑ አሶሳ ሲገቡም የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንና በከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
 
የሁለቱ ሃገራት ክልሎች ባለፉት ዓመታት በልማትና በሠላም ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ስምምነት ተፈራርመው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
 
በዛሬው ውይታቸውም ያለፈውን የጋራ ሥራ በመገምገም የጀመሯቸውን ስራዎች በሚያጠክሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡
 
በመድረኩም የፌዴራልና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግስትና የጸጥታ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.