Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማዋን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ያስችላል ያለውን ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የከተማ መሬት ይዞታ ሊዝ ክፍያ ውዝፍ ዕዳ ማቅለያ እንዲሁም የአልሚዎች የግንባታ መጀመረያና መጨረሻ ጊዜን አሥመልክቶ የተለያዩ ውሣኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት በሊዝ የተያዙና ከአሁን ቀደም አግባብ ባለው አካል የይዞታ ማረጋገጫ በሊዝ ስርዓት እንዲሥተናገዱ በተወሠነላቸውና በቀጥታ በሊዝ በተያዙ የመኖሪያ ይዞታዎች ላይ በአልሚዎች ተይዘው የሊዝ ክፍያ ፍሬ ግብር እንዲከፍሉ ነገር ግን ወለድና ቅጣት እንዲነሳላቸው ውሳኔ አሳልፏል።

መሬት አግባብ ባለው የሊዝ ሥራአት ወስደው በወቅቱ ግንባታ ያልጀመሩና ያላጠናቀቁ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም ተቋማት የግንባታ ፈቃዳቸውን ያለቅጣት እንዲያድሱና ተጨማሪ የአንድ ዓመት የማራዘሚያ ጊዜ እንዲሰጣቸውም ብሏል።

በሪልስቴት ከተያዙት ውጪ የመኖሪያ ይዞታዎች ወለድና መቀጫ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳላቸውም ነው ውሳኔ ያሳለፈው።

ለቢዝነሥ በተለይም በሆቴልና ቱሪዝም ይዞታዎች መቀጫን ሙሉ ለሙሉ ወለድ ደግሞ 30 በመቶ እንዲቀር የተወሰነ ሲሆን ውሣኔው የከተማ አስተዳደሩን እሥከ 1 ቢልየን ብር ገቢ የሚያሣጣ መሆኑ ነው የተመለከተው።

ያም ቢሆንም የተቀዛቀዘውን የከተማዋን ኢኮኖሚ በተለይም የግንባታ ዘርፋን በማነቃቃት ረገድ ከሚኖረው ሚና ባሻገር ውዝፍ ገቢዎች እንዲሠበሠቡ የሚያሥችልና ከ50 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ ውሣኔ እንደሆነ ካቢኔው ተመልክቷል፡፡

በክስ ሂደት ላይ ያሉ አልሚዎችም ከቅጣቱና ከወለድ ክፍያ 30 በመቶ ተነስቶላቸው እንዲከፍሉ ተወስኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.