Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ትምህርት ያሰለጠናቸውን 209 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣የካቲት 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 209 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ተገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ጣሰው እጩ ምሩቃኑ ላለፉት ስድስት ዓመታት የሕክምና ትምህርታቸውን በትጋት በመከታተል በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንዲሁም ተማሪዎች በቅንነት፣ በሃቀኝነት እና በታማኝነት ሀገራቸውን ማገልገል እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው፥ የሕክምና ሙያ ሃላፊነቱ የገዘፈ ጥንቃቄና ፅናት የሚሻ መሆኑን በመግለጽ እንደ ማንኛውም የሙያ መስክ አንዱ የስልጠና ምእራፍ ሲዘጋ ሌላው እየተከፈተ እንደሚሄድ አንስተዋል።

ሙያው እየረቀቀ የሚሄድ፣ በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆነና ዘመኑ ካፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ጋር ራስን ማራመድ የሚጠይቅ በመሆኑ ተማሪዎች እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለማዳበር ጥረታቸውን ሳያቋርጡ መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.