Fana: At a Speed of Life!

የኢኮኖሚና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በየሴክተሩ ያሉ የአሰራር ክፍተቶች እየተለዩ ነው- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኮኖሚና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በየሴክተሩ ያሉ የአሰራር ክፍተቶች እየተለዩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

አቶ ሽመልስ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ችግሮቸን ለመቅረፍ በማለት በአዲስ አበባ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ ላይ በኦሮሚያ ክልል ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ከባለሀብቶች ጋር ምክክር መደረጉን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ በመድረኩ ላይ በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ቸግሮችን ለመቅረፍ መቀመጫውን ብሪታኒያ ካደረገው ቢግ ዊን ፋውንዴሽን እየተሰራ ነው ብለዋል።

የተጓተቱ የኢንቨስትመንት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ስራ ማስገባት እና አዳዲስ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ እየሰጡ መሄድ ወሳኝ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

እስካሁን በ66 ሴክተሮች ውስጥ ያሉ ችግሮችን የመለየት ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ይስ ስራ ቀጣይነት ያለው መሆኑነም አስታውቀዋል።

ተመሳሳይ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ዘርፉን ለማበረታታት የግሉ ሴክተር ሚና መሳኝነት አለው ሲሉም ተናግርዋል።

የተለዩ ችግሮች ላይ ጥናት በማድረግ መፍትሄ በመስጠት ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር ደግሞ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.