Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከ20 ሺህ በላይ መጻሕፍት አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከ20 ሺህ በላይ መጻሕፍት አበረከተ።

ከዚህ ውስጥ 13 ሺህ 260 የሚሆኑት መጻሕፍት የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የጥበብና የባህል መጻሕፍት ናቸው።

መጻሕፍቱ አፋን ኦሮሞን ጨምሮ በሦስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በርክክብ መርሃ-ግብሩ ላይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱላኪም ሙሉ ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፥ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በፈለጉት ቋንቋ ማንበብ የሚችሉበት ትልቅ ቤተ-መጻሕፍት በመሆኑ ወደፊት በሀገሪቱ በተለያዩ ቋንቋዎች የተፃፉ መጻሕፍት በግብዓትነት የሚካተቱ ይሆናል ብለዋል::

ዜጎች በዕውቀት እና በምክንያት እያሰቡ ለሀገራቸው ዕድገት እና ብልፅግና የበኩላቸውን እንዲወጡ የተበረከቱት መጻሕፍት የላቀ ሚና እንዳላቸውም ተገልጿል።

በአዲሱ ሙሉነህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.