Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነት ነፃነቷን ማስጠበቋን ያረጋግጣል – የአርባምንጭ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግንባር መዝመት ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሰዋእትነት ነፃነቷን አስጠብቃ የኖረች መሆኗን የሚያረጋግጥ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግንባር መዝመት ለኢትዮጵያ ልዕልና የሚኖረው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የመሪያቸዉን ፈለግ በመከተል አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ባለፈ ግምባር በመዝመት ነፃነትን ለመቀዳጀት መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ክህደት የፈፀሙባትን የውስጥ ባንዳዎችና የዉጪ ወራሪዎችን በመመከትና ድል በመቀዳጀት የማይሻር ታሪክ ፅፋለች የሚሉት የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ÷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ይህንን የሚያሳይ አንደሆነ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ነፃነቷን ይዛ መቆየቷ ከክብራቸው ይልቅ ሀገርንና ህዝብን የሚያስቀድሙ መሪዎችና ህዝቦች በከፈሉት መሰዋእትነት ነው ማለታቸውን የዘገበው ደሬቴድ ነው።

እኛም ለሀገር ምንም ሳንሰስት ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን ሲሉም አረጋግጠዋል ነዋሪዎቹ።

ትግሉ በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ በአካባቢያችን ተላላኪዎችን በግንባር ደግሞ ከሃዲዎችን እንፋለማለንም ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እዉነተኛ የሀገር ወዳድና ባለውለታ መሆናቸውን በአደባባይ ማረጋገጣቸውን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ ÷ ከልማት ስራው ጎን ለጎን ለኢትዮጵያ ነፃነት እንታገላለን ድልም እንቀዳጃለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዛሬም ነፃነቷን የሚያስከብሩ የጀግኖች ሀገር ናት ያሉት የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ÷ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግንባር መዝመት የኢትዮጵያን ልዕልና ከማረጋገጥ ባሻገር በርካቶችን እንደሚያጀግንም እምነታቸውን ገልፀዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.