Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች 12ኛውን የጋራ ጉባዔያቸውን በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄዱ ነው።
በኮሚሽነሮቹ የጋራ ጉባዔ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተገኙ ሲሆን÷ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች ታድመዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ በፌደራል ፖሊስ መዋቅራዊ አደረጃጀት እንዲሁም የማዕረግ ዕድገት አሰጣጥና ስያሜ ችግሮችና መፍትሔዎችን የሚያመላክት የጥናት ሪፖርት ይቀርባል።
ከፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ ጥራትና አቅርቦት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ችግሮችና መፍትሔዎች እንዲሁም በኮሚሽኑ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት እንደሚካሄድም ታውቋል።
በጉባዔው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የጉባዔው ዓላማ የሃገሪቱን ፖሊስ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ መሆኑን ገልፀዋል።
በጉባዔው ፖሊሱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የሚፈቱባቸውን መንገዶች የሚያመላክቱ ጥናቶች ይቀርባሉም ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እንድትቀጥል መስዋዕትነት የሚከፍልላት ሠራዊት እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል።
ይህንንም የመከላከያ ሠራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊሶች በተግባር ማስመስከራቸውን ገልጸዋል።
የሕግ የበላይነት እንዲከበርና እኩልነት እንዲረጋገጥ የፖሊስ ሚና የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ጉባዔው ነገም የሚቀጥል ሲሆን በክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የስድስተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የሚያመላክት ዕቅድም በነገው ዕለት እንደሚቀርብ ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.