Fana: At a Speed of Life!

የ ’በቃ’ ዓለምአቀፍ ንቅናቄ ዘመቻ አካል የሆነው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በእየሩሳሌም እና በስፔን ባርሴሎና ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆነው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በእየሩሳሌም እና በስፔን ባርሴሎና ተካሄደ።
በዛሬው እለት በሀገረ እስራኤል እና በእስፔን ባርሴሎና የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዓለማቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore‘ ዘመቻ አካል የሆነውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ኤርትራውያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች በንቅናቄው በመሳተፍ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ አገራት በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት ሰልፈኞቹ አውግዘዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች የፈጸማቸው ግፍና በደሎች እንዲቆሙ የሁሉም ርብርብ እንደሚጠበቅ የገለጹት የንቅናቄው ተሳታፊዎች፥ አሸባሪው ቡድን የፈጸማቸው ኢሰብዓዊ የሆኑ እኩይ ድርጊቶች በወንጀል የሚያስጠይቁ እንደሆኑና ይህን ግፍና በደል በዝምታ ማለፍ ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
ምዕራባውያንም የኢትዮጵያውያንን ድምፅ እንዲሰሙና የአሸባሪውን የትህነግ ድርጊት በማውገዝ ለፍርድ እንዲቀርብ እንዲተባበሩ ሰልፈኞቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ ሰልፍ”’ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጎን ቆመናል፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግስት ማክበርና ለሚወስደው ሕጋዊ እርምጃ ድጋፍና እውቅና መስጠት አለበት” የሚሉና ሌሎች ‘የበቃ’ እንቅስቃሴ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በእስራኤል የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ እና የቀድሞ የእስራኤል ፓርላማ አባል የሆኑት ሽሎሞ ሞላ ባሰሙት ንግግር፥ “እኛ በእስራኤል አገር ያለን ቤተ-እስራኤላውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አያት ቅድመ-አያቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው ያቆሟት ኢትዮጵያ ፥ እትብታችን የተቀበረባት ስለሆነችነ በልባችን ውስጥ ናት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
“ሰልፍ የወጣነው ትውልድ አገራችን ኢትዮጵያ ስትነካ ቁጭ ብለን አናይም ብለን ነው” ያሉት ሽሎሞ ሞላ ፤ ስለዚህም ለእውነት እና ለፍትህ ስንል በታላቅ ፍቅርና ተስፋ ለኢትዮጵያ ሰላም የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።
በሁለቱም ሰልፎች የተሳተፉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ኤርትራውያን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች በመገኘት ለወገኖቻቸው ያላቸውን አጋርነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.