Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በምርጫው ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በመጪው ግንቦት ስለሚካሄደው ምርጫ መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎች መቀመጣቸውን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ ምርጫ የመንግሥት ኃላፊነት ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው ብለዋል።

በዚሁ መሠረት፣ የክልል ብሔራዊ መንግሥታትም በምርጫው ሂደት ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማገዝ ቁርጠኝነትን ማሳየታቸውንም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.