Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ግንባር ማቅናታቸው የዚህ ትውልድ ታሪክ ሆኖ ሊጠራ ይችላል – የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተከፈተባትን ጦርነት ለመምራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር ማቅናታቸው በዚህ ትውልድ የተፈጸመ የመጀመሪያ ታሪክ ሆኖ ሊጠራ የሚችል ተግባር ነው አሉ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርአያነት ውሳኔ በግንባር ለሚፋለሙ ጀግኖች የሞራል ስንቅ በመሆን ድልን ለማስመዝገብ የተወሰደ ትልቅ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል።
በግንባር ያለው አመራር እና ሰራዊት ቀን ከለሌት ያለእረፍት ህይወቱን ጭምር በመሰዋት እየሰራ በመሆኑ፥ “በማዕከል የምንገኝ አመራሮች እና ሰራተኞችም አሁን አገርን ለማዳን መደበኛ የስራ ሰዓት ሳንገደብ በኢኮኖሚው ዘርፍ መረባረብ አለብን” ነው ያሉት።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦሩን ለመምራት ወደ ግንባር ማቅናት በህዝቡና በአመራሩ ላይ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩን አንስተዋል።
ጦርነቱ ኢትዮጵያን የማጽናት እና የመበተን መሆኑን የተረዳው የመዲናዋ ነዋሪም ወደ ግንባር ከመዝመት ጀምሮ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ወደ ግንባር ከሚያቀኑት አመራሮች ውጪ ቀሪዎቹ አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ባህልን በሚቀይር መልኩ ሃላፊነታቸውን ለመወጣትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አርአያነት ለመድገምም ተዘጋጅተዋል ብለዋል ምክትል ከንቲባው።
በበላይ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.