Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ የአቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ የአቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች መዝገብ የአቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ችሎት ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም፥ አምስት ተጠርጣሪዎች ከህክምና ጋር በተያያዘ ስላልቀረቡ እነሱ በሌሉበት ምስክሮች ሊሰሙ አይገባም የሚል አቤቱታን ተጠርጣሪዎቹ አቅርበው ነበር።

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶበታል።

በዛሬው ችሎት ከስምንት የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን የተገኙ ጋዜጠኞች ችሎቱን እንዲከታተሉ የተደረገበት የፕላዝማ ቴሌቪዥን አገልግሎት ባለመስጠቱ መከታተል አልተቻለም ነበር።

ሆኖም ከአቃቤ ህግ እና ከተጠርጣሪ ጠበቆች እንደተረዳነው አቃቤ
ህግ ያቀረበውን የምስክርነት ይሰማልኝ ተለዋጭ ቀጠሮን ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የአቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ሰኞ ነሃሴ 11 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎች ከቤተሰብ ጋር እንድንገናኝ እና ምግብ ቢገባለን የሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ በጥንቃቄ ከቤተሰብ ጋር እንዲገናኙ እንዲደረግ አዟል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.