Fana: At a Speed of Life!

ሰበር ዜና፤ የወገን ጦር ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሸናን ግንባር ምሽጎች ደርምሰው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጠሩ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ÷በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ለማስመዝገብ በመቻሉ ነው ብሏል፡፡
ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ራሳቸውን በጠላት እንዳላስደፈሩት የግዳንና የራያ ወረዳዎች ሁሉ ቀሪዎቹ በወረራ ሥር የሚነገኙ የዋግ ሕምራ፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ሕዝብ፣ ከጀግኖቹ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጠላትን እንዲደመስስና ነጻነቱን እንዲያስከብር መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.