Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስሑል ሽረ፣ አዳማ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል። ኢትዮጵያ ቡናን በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ያስተናገደው አዳማ ከተማ ደግሞ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዳዋ ሆቴሳ እና ከነዓን ማርክነህ አስቆጥረዋል። በትግራይ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ስሁል ሽረ 3 ለ 0 በሆነ…
Read More...

ቢሾፍቱ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች የአለምዘርፍ የኋላና በወንዶች ታምራት ቶላ አሸፈንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ  ከተማ ዛሬ በተካሄደው13ኛው የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን ውድድር   በሴቶች አትሌት የአለምዘርፍ የኋላ እንዲሁም በወንዶች ታምራት ቶላ ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል። ውድድርሩ  ፖላንድ ለሚካሄደው የአለም የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን  ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።…

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የቡሩንዲ አቻውን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ከቡሩንዲ አቻው ጋር ተጫውቷል። ቡድኑ የቡሩንዲ አቻውን 2ለ1በሆነ ውጤት አሸንፏል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦች ሥራ ይርዳው በ27 ኛው እና አረጋሽ ከልሳ በ30 ኛው…

በአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 7 ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ፍጻሜውን ባገኘው የአፍሪካ ልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 7 ሜዳሊያዎች በማግኘት አጠናቃለች። የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር በግብጽ ካይሮ፥ በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በቦሽያ ስፖርት ተካሄዷል። ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ ስፖርት…

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የመጀመሪያዋን ጎል በ21ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ…

የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኮሮና ቨይረስ ምክንያት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና አስተናጋጅነት በናንጂንግ ሊካሄድ የነበረውን የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀገሪቱ በተከሰተው በኮሮና ቨይረስ ምክንያት መራዘሙ ተገለፀ። የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቻይናዋ ናንጂንግ ከተማ አስተናጋጅነት ከፊታችን ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 6 ድረስ እንደሚካሄድ ነበር…

በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ተካሂደዋል። የፕሪሚየር ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ መቐለ ላይ ከስሑል ሽረ ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ወደ ጅማ አቅንቶ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር 0…