Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የቀድሞው የካፍ ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ግብፃዊው አምር ፋህሚ በካንሰር ህመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፥ በ36 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፋህሚ ከፈረንጆቹ 2017 እስከ 2019 ድረስ የካፍ ዋና ፀሃፊ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ቀደም ባሉት አመታትም ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ፕሬዚዳንት ሆነው መርተዋል። ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮችን በበላይነት ያስተዳደሩ ሲሆን፥…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና ባህርዳር ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ባህርዳር ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። ወላይታ ድቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። ሰበታ ከተማን በሜዳው ያስተናገደው  ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማን  1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሲዳማን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም  ይገዙ ቦጋለ በ56ተኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል። የሊጉ በርከት ያሉ ጨዋታዎችም ነገ የሚካሄዱ ይሆናል።

በፕሪሚየር ሊጉ ሃዲያ ሆሳዕና ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ ተካሄዷል። በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና በጅማ አባጅፋርን በሃዋሳ ስታዲየም አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሃዲያ ሆሳዕናን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል አዩብ በቀታ ማስቆጠር ችሏል። ሌሎች የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ…

አትሌት አባብል የሻነህ በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ከሂማህ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች። አትሌት አባብል በፈረንጆቹ 2017 ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ በቫሌንሺያ የያዘችውን ክብረ ወሰን በ20 ሰከንድ በማሻሻል አሸንፋለች። በውድድሩ አትሌት…