Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ማጠናቀቅ የ2015 ዓ.ም ትኩረት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የህብረተሰቡ ቅሬታ የሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ማጠናቀቅ የ2015ዓ.ም ትኩረት መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ።
ከፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ÷ ግንባታቸው የተጓተቱ እና የህብረተሰቡ ቅሬታ ምንጭ የሆኑ የመንገድ ግንባታዎች ለማጠናቀቅ ግብ መቀመጡን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ግንባታው በ3 አመት ይጠናቀቃል ተብሎ ሳይጠናቀቅ 5 አመታት ያለፈው የቃሊቲ ቱሊዲምቱ መንገድ ፕሮጀክት ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ቀዳሚ ነው ብለዋል።
በብድር አለመለቀቅ የዘገየውን ይህን መንገድ በ2015ዓ.ም በራስ አቅም ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ለማድረግም እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በአመቱ እንዲጠናቀቁ ከሚደረጉት ውስጥ የኮተቤ – ካራ መንገድ ፕሮጀክት አንደሚገኝበትም ተመላክቷል፡፡
እንደ ዋና ዳሬክተሩ ገለጻ በ2015ዓም አመት ግንባታቸው የተጀመሩ 25 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅም ታቅዷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲስ የሚጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩም ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ ተናግረዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.