Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን በቀጠናው የሚገኘው የክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ገለፁ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና፣ ኪረሙ፣ በኢበንቱ፣ በሀሮሊው እና በሊሙ ወረዳዎች ዙሪያና አካባቢው በአሸባሪው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እየተወሰደበት እንዳለ ተገልጿል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኘው የክፍለ ጦር ዋና አዛዥ እንዳሉት÷ በአሸባሪው የህወሃት ሳንባ በሚተነፍሰው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ በተወሠደው የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ 49 የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ሲማረኩ፣ አምስቱ እርምጃ ተውስዶባቸዋል 50 የሚሆኑት ጀሌዎች ደግሞ ለሽብር ቡድኑ መረጃ ሲያቀብሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ አሸባሪው ሸኔ ከሕዝብና ከመንግሥት ተቋማት ዘርፎ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 18 ሞተር ሳይክሎች፣ 44 ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ 26 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ 25 በርሜል ነዳጅን ጨምሮ 74 ሺህ 795 ብር መያዙን ተናግረዋል።

ዋና አዛዡ አክለውም÷ ክፍለ ጦሩ በስፍራው ከመድረሱ በፊት የአሸባሪው ሸኔ ቡድን በአካባቢው ማህበረሠብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ስቃይና እንግልት ያደርስ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ሠራዊቱ ይህን የጥፋት ቡድን የመደምሰስ ግዳጅ ተቀብሎ ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ግዳጅ መፈፀም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በአምስት ወረዳዎች ጠላትን በመደምሠስ የአካባቢውን ሠላም መመለስ መቻሉ ተገልጿል።

የአሸባሪው የወያኔ ተላላኪ ክንፍ የሆነውን የሸኔ ቡድንን ለመደምሰስ በተደረገው የተጠናከረ ዘመቻ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጋቲራ ቀበሌ ከህዝቡ ተዘርፈው የተወሰዱትን 40 የቀንድ ከብቶች ለባለቤቶቻቸው መመለሳቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.