Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል እስካሁን ድረስ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር መሬት በዘር መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርት ዘመኑ እስካሁን ባለው መረጃ በአማራ ክልል 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታሩ በኩታ ገጠም እርሻ እየለማ ያለ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታር መሬቱ በዘር ተሸፍኗል ብሏል፡፡

በአማራ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ወቅት 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማልማት ከ143 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ለመኸር እርሻ ከተዘጋጀው መሬት ውስጥ 304 ሺህ 681 ሔክታር በትራክተር ማረስ እንደተቻለና 12 ለገበያ የሚውሉ ሰብሎች በዋናነት እንደሚመረቱም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.