Fana: At a Speed of Life!

በአረብ ኤምሬቶች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን ህጋዊ ለማድረግ ከስምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን ህጋዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝታቸውን ዛሬ ያጠናቅቃሉ።

ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረትም የጉዞ ሰነድ በማጣት እና በከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ከሀገር እንዳይወጡ ለዓመታት ተከልክለው የቆዩ 135 ኢትዮጵያውያንን ይዘው ይመለሳሉ።

ከአርብ ጀምሮ በሀገሪቱ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስሩ፥ ከተለያዩ የአረብ ሀገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል።

ያንንም ተከትሎ ከሀገሪቱ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በእነዘህ ውይይቶች በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ያሉባቸው ችግሮች እንዲፈቱ ከስምምነት መደረሱንም ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ያስታወቁት።

ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ለመክፈት ከስምምነት ተደርሷል።

በጉዞው በተደረገ የዲፕሎማሲ ስራ በአቡዳቢ ለኢትጵዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰሪያ ቦታም ተፈቅዷል።

በዱባይ እና ሻርጃ ግዛቶች አማካይ ስፍራ ለፕሮቴስታንት አማኞችም የጸሎት ቦታ በኤክስፖ 2020 ከሚሰራ ህንፃ እንዲሰጥ መወሰኑን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በሁሉም መስክ እጅግ የተሳካ መሆኑን አቶ ንጉሱ ገልጸዋል።

 

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.