Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ቴአትር የተጀመረበት 100ኛ ዓመት የሚዘክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ቴአትር የተጀመረበት 100ኛ ዓመት የሚዘክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ የኢትዮጵያ ቴአትር ባለሙያዎች ማህበር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴአትር ዲፓርትመንት መምህራንና ተማሪዎች ፣ የቴአትር አድናቂዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትብብር ተዘጋጅቷል፡፡

መርሃ ግብሩ ‘‘ቴአትር በኔ ዘመን አይሞትም’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለተከታታይ አንድ ወር 100 ቴአትሮች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
አላማውም በኮቪድ-19 ምክንያት የተዳከመውን የቴአትር ዘርፍ ለማነቃቃት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመርሃ ግብሩ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አንጋፋና ወጣት የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የቴአትር አድናቂዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ‘‘ሼክስፔር ኢትዮጵያዊ ነው’’ እና ‘‘የካሳ ፈረሶች’’ የሚሉ ቴአትሮች ለታዳሚያን የቀረቡ ሲሆን፤ የፎቶ አውደርዕይ በመርሃግበሩ ለዕይታ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.