Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በቀን ከ 1 ሺህ ዩኒት በላይ ደም እየተሰበሰበ ነው

አዲስ አበባ፣ግንቦት 27 ፣2012  (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚ ክልል በሚገኙ አስር የደም ባንኮች በቀን እስከ አንድ ሺህ አንድ መቶ ዩኒት ደም እየተሰበሰበ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ጤና  ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ÷በኮሮና ወረርሽኝ  ምክንያት በመደበኛ የጤና አገልግሎት ሂደት ባገጠመው የደም እጥረት በተለይ እናቶችና ህፃናት እንዳይጎዱ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በዚህም በክልሉ በሚገኙ 10 የደም ባንኮች  በቀን  ከ850 እስከ 1ሺህ 1 መቶ ዩኒት ደም እየሰበሰቡ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

ባለፈው አንድ ወር በተደረገው ዘመቻ ከ30 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች መሰብሰብ መቻሉን  ዶክተር አብዱልቃድር ገልጸዋል።

ይህም በክልሉ ጤና ተቋማት የደም ፍላጎት እጅጉን የሚያስፈልግ በመሆኑ እጥረት እንዳይኖር  ለማስቻል እንደሚያግዝም ነው ብለዋል ።

በተለይም የደም እጥረት በሚኖርባቸው ቦረና፣ ጉጂ፣ አራቱ የወለጋ ዞኖችና ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ባሉት የጤና ተቋማት በቂ ደም ካላቸው ባንኮች ወስደው በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በወሊድ ምክንያት የሚፈሰውን ደም ለመተካት፣  እንዲሁም ሌሎች ደም የሚፈልጉ ታካሚዎችን ለመታደግ ጭምር እየተሠራ መሆኑን የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊ  አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን አባላት ትናንት በአዳማ ከተማ በመገኘት ደም በመለገስና በኮሮና ምክንያት በተገደበው እንቅስቃሴ ለተቸገሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች  የምግብ ዘይትና የስንዴ ዱቄት ድጋፍ  ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.