Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ፀሃፊ ጃኒን አልም ኤሪክሰን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም አምባሳደር ድሪባ መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያላትን ዝግጁነት በተመለከተ አብራርተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ ውይይት ከመጀመሩ በፊት ሱዳን የያዘችውን መሬት በፍጥነት ለቃ እንድትወጣ ፍላጎቷ መሆኑን አስረድተዋል።

የስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ፀሃፊ ጃኒን አልም ኤሪክሰን በበኩላቸው መንግስት ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የትግራይ ክልልን ክፍት ማድረጉን አድንቀዋል።

ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ክልል አሉ ከተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ ላወጣው ሪፖርት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አያይዘውም በክልሉ የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በውይይቱ ወቅት በሁለቱን ሃገራት መካከል ያለውን የልማት ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.