Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ያስተባበራቸው 12 የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሀገር- በቀል ችግኞችን ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ያስተባበራቸው 12 የመንግስት የልማት ድርጅቶች በየም ልዩ ወረዳ ሳጃ ከተማ በአራተኛው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሀገር በቀል ችግኞችን ተከሉ።

በደቡብ ክልል የም ልዩ ወረዳ ሳጃ ከተማ ላይ የተካሄደው የችግኝ ተከላ የአራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካል ሲሆን ፥ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ለአካባቢ ተስማሚ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።

ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ በስሩ የሚያስተዳድራቸው አብዛኞቹ ተቋማት ኢንዱስትሪዎች በመሆናቸው ወደ ከባቢ አየር የሚለቁትን የካርበን መጠን ለመታደግ በሚያስችል መልኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ መከናወኑ ተገልጿል ።

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ምሳጋኑ አረጋ እንደገለፁት በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ የችግኝ ተከላው በየም ልዩ ወረዳ መከናወኑ የፌዴራል ተቋማት ከተለያዩ ወረዳዎች ጋር ተቀራርበው ለመስራት ያስችላቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም ካርበን የምናመነጭ ትላልቅ ተቋማት ለአረንጓዴ አሻራ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት አለብንም ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በየም ልዩ ወረዳ የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት አስጀምረዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አስተባባሪነት የመንግስት የልማት ድርጅት የሆኑት የኮንስትራክሽንና ዲዛየን ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ሌሎች የበርካታ ተቋማት ሥራ አስፈፃሚዎችና ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.