Fana: At a Speed of Life!

ከገረገራ እስከ ጋሸና ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከገረገራ እስከ ጋሸና ያለውን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ፡፡

ከህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደ የፍተሻ ሥራ 34 በሚሆኑ ታወሮች መካከል በሚገኙ ቦታዎች ላይ 50 የመስመሮች መበጣጠስ፣ 7 የድምፅና ዳታ ማስተላለፊያ የኦፕቲካል ፋይበር መቆረጥ እና 13 ቦታዎች ላይ መስመር ሳይበጠስ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ሥር በምትገኘው የአርቢት ቀበሌ ባለ 3 ፌዝ መሥመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር ላይ ከፍተኛ መበጣጠስ መድረሱ ተመላክቷል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸው መስመሮች ላይ ጥገና የተጀመረ ሲሆን፥ ጥገናውን በፍጥነት በማጠናቀቅ አካባቢዎቹ ኃይል ማግኘት እንዲችሉ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛልም ነው ያለው፡፡

ከዚህ ቀደም አሸባሪው ህወሃት ጉዳት ያደረሰባቸውን ከደብረታቦር እስከ ገረገራ ባሉት አካባቢዎች ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.