Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጭና የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአርባምንጭና የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ነገ ለሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ፡፡
በጋሞ ዞን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ለራሳቸው የሚሆነውን ፖርቲ ለመምረጥ የተዘጋጁ ሲሆን ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ለምርጫ ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል ።
በሌላ በኩል በነገው እለት ከሚካሄዳው ምርጫ ጎን ለጎን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደሚካሄድ የጋሞ ዞን አከባቢ ጥበቃ እና ደን ልማት ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መዓዛ ሽቀነ ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ የአርሲ ዞን የአሰላ ከተማ ነዋሪዎችም የጥሞና ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ነዋሪዎቹ ይበጀናል የሚሉትን ፖርቲ ለመምረጥ ነገን እየጠበቁ መሆኑን ተናግረው ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡
በአርሲ ዞንና በከተማው ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ 1ሚሊየን 526ሺህ 987 መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡
ስድስት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በዞኑና በከተማው ለምርጫው መቅረባቸው ታውቋል፡፡
በማቲዎስ ፈለቀና በኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.