Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር የነበሩት ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር የነበሩት ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው።
ተጠርጣሪዎቹ ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊ ፣የቀድሞ የመከላከለያ ጡረተኛው ሌተናል ኮሎኔል ገብረማርያም አርያ ፣ ወይዘሮ ተክለብርሃን በርሄ፣ ዘረሰናይ ገብረዮሀንስ፣ የቀድሞ የመከላከለያ ጡረተኛው ብርጋዴል ጀነራል ሀየሎም ግብረስላሴ እና ዳንኤል ገብረመድህን ይባላሉ።
ተጠርጣሪዎቹ ላይ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ዋስ ፈቅዶላቸው የነበረ ሲሆን መርማሪ ፖሊስም በይግባኝ መዝገቡ እንደገና እንዲታይ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ የሰራውን የምርመራ ስራ የገለጸ ሲሆን÷ ተጠርጣሪዎችም 53 ቀን ሙሉ ያለአግባብ ታስረናል ሲሉ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
መዝገቡን የመረመረው ፍርድ ቤትም የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጠው የወንጀል ተሳትፎ አጣርቶ ማስረጃ ለማቅረብ እንጂ ተመሳሳይ ምርመራ ለማቅረብ አይደለም ብሏል።
ተጠርጣዎቹም 53 ቀን የታሰሩ በመሆኑና የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን ባገናዘበ መልኩ ምርመራው ያልተሰራ በመሆኑ እንዲሁም ፍርድ ቤት የተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት እና የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የማስከበር ሀላፊነት ያለው መሆኑን በምክንያትነት ጠቅሶ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
ከዚያም ባለፈ ከዚህ በፊት ችሎት ያስያዙት የዋስትና ብርም ካለ እንዲመለስላቸው ፍርድ ቤቱ የወሰነ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹም ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል አዟል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.