Fana: At a Speed of Life!

የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ተግባራዊነት ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ተግባራዊነት ላይ ውይይት ተደረገ።

በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው ውይይት ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚፈጠሩ ስጋቶች ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ የጦር መሳሪያ ባለቤት ለመሆን ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ ተነስቷል።

ከዚህ ባለፈም በድንበር በኩል በህገ ወጥ መልኩ እየገባ ያለው የጦር መሳሪያ እየጨመረ መሆኑም ነው የተነሳው።

ለዚህም እንደ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ያሉ ጎረቤት ሃገራት አለመረጋጋት በድንበር በኩል ለሚገባው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መጨመር ምክንያት ነው ተብሏል።

ውይይቱም በጦር መሳሪያ አስተዳደር ዙሪያ የሚነሱ ሃሳቦችን እንደ ግብዓት በመጠቀም የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።

የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ባለፈው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል።

አዋጁ ተገቢው ምዝገባ ተደርጎ በህጋዊ መልኩ የጦር መሳሪያን ለማስተዳደር እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ባለድምፅ መሳሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ለድምፅ አልባ የጦር መሳሪያዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሏል።

በሹመት አለማየሁ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.